ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኦሮሞ ሕዝብ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ የሚገጥሟቸውን ችግሮች ሲፈታበት የቆየው የሽምግልና ፍርድ ህጋዊ ሊሆን ነው ተባለ።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በሽማግሌዎች ፍርድ የተበደ የሚካስበትና እውነተኛ ፍርድ የሚሰጥበት የማኅበረሰቡን  የቆየ እሴት የሕግ እውቅና ባለው መንገድ እንዲሠራ ለማድረግ ባሕላዊ ፍርድ ቤት እያቋቋመ መሆኑን የኦሮሚያለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይፋ አድርጓል።
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሙኑኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክተር አቶ ጎንፋ አቶማ ፤ ይህ የሚቋቋመው ባሕላዊ ፍርድ ቤት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን ጫና የሚያቃልል እንደሆነ ከመጠቆማቸው ባሻገር፤ “ባሕላዊ ፍርድ ቤት ማለት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ባሕላዊ እሴት በመጠቀም ግጭቶቹን በፍርድ ቤት መፍታት ማለት ነው። ፍርድ ቤቱ የሚጠቀማቸው የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ሕግ ሳይሆን ባሕላዊ ሕጎችን ነው።” ብለዋል።
የባሕላዊ ፍርድ ቤት አመሠራረትም የፌደራል እና ክልልን ሕገ መንግሥትንና እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ምሥረታ እና ሥልጣን ድንጋጌ 216/11 መሠረት ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY