በትግራይ የትራንስፖርት እና የመጠጥ ውኃ ዋጋ በእጅጉ ጨመረ

በትግራይ የትራንስፖርት እና የመጠጥ ውኃ ዋጋ በእጅጉ ጨመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑና መንግሥትም እየወሰዱኩ ነው ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በፍጥነት ባለማጠናቀቁ በክልሉ የትራንስፖርት ዋጋ በእጅጉ ለመናር ተገዷል።

በክልሉ በተካሔደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንቅስቃሴዎች በመገታታቸው ምክንያት ከመቀሌ አላማጣ የሚጓዙ መንገደኞች 800 ብር እየከፈሉ ነው ተብሏል።
ከመቀሌ አላማጣ የሚደርሰው መስመር ርዝመት 177 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ ቀደም ሲል መደበኛ የታሪፍ ዋጋው 90 ብር ቢሆንም አሁን ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች መንገደኞችን ከመደበኛው ታሪፍ በላይ የ700 ብር ጭማሪ እያስከፈሉ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በሚስተዋልባት መቀሌ በአነስተኛ ምግብ ቤቶች ውስጥ አንድ በየአይነት (የጾም ምግብ) መቶ ሀያ ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፤ ዐሥር ሊትር የሚይዝ ጀርኪን የቧንቧ ውሃ በአርባ ብር  እየተሸጠ እንደሚገኝ፣ የውሃ አቅርቦቱም ባሳምንትና በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ብቻ የሚታይ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

LEAVE A REPLY