የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያዘጋጀው የ10 ዓመታት የልማት እቅድን የፓርላማው አባላት ተወያዮበት

የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያዘጋጀው የ10 ዓመታት የልማት እቅድን የፓርላማው አባላት ተወያዮበት

PM Netanyahu addressing the Ethiopian parliament

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ባዘጋጀው የ10 አመታት የልማት እቅድን በተመከለተ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት ተደረገ።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የሚደረገው የ2 ቀናት ውይይት የውይይቱ አካል እንደሆነም ተነግሯል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እቅድ ወዳሰብነው ውጤት ሊያደርሰን የሚችል መሳሪያ መሆኑን ጠቁመው፤ ከለውጡ በፊት በነበረው ጊዜ ሕዝቡን ለማድመጥ ባለመቻላችን በርካታ ችግርች ተከስተዋል ብለዋል።
የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ባለፉት አመታት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ጨምሮ በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ የ10 አመቱን እቅድ አስፈላጊነት እንዲሁም ልዩ ባህሪያትን ለተወያዮች አብራርተዋል። ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ከ2013 እስከ 2022 የበጀት አመታት ድረስ ያለው የ10 አመት የልማት እቅድ ሰነድ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ታህሳስ 2 ቀን 2013 መፅደቁ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY