ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቋቋሙት ግብረ ኃይል የመተከል ዞን ፀጥታ ማስከበርን ተረከበ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቋቋሙት ግብረ ኃይል የመተከል ዞን ፀጥታ ማስከበርን ተረከበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ሥራ መረከቡን ሜጀር ጀነራል አስራት ዴኔሮ ገለጹ።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል ነው የተባለው።
የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሜጀር ጀነራል አስራት ዴኔሮ  የንፁሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ሥራው እንደቀጠለ ጠቁመው፤
በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ ሲሉም ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY