ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሠራ እነደሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።
አምባሳደር ዲና የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየሠራ ነው ያሉት ቃል አቀባዮ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተው በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል።
ሱዳን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ህግ በምታስከብርበት ወቅት ሱዳን የዲፕሎማሲ ድጋፏን አሳይታለች፤ ዜጎች ሲሰደዱም አስተናግዳለች፤ ይሄም እንደ በጎ ሊታይ ይገባል ያሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤
አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ ውጥረቱ ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ እንዲፈታ መንግስት እየሠራ እንደሆነና በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ግጭት ሀገራት የቀደመ ታሪክ የማይመጥን እንደሆነም በመግለጫው ተጠቁሟል።