ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ አለ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በእስክንድር ነጋ የሚመራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ በቅርብ ቀን በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ አለ።

በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገሪቱን በቅጡ ማስተዳደርና የሕዝቡንም ሰላም ማስጠበቅ አልቻለም ያለው ባልደራስ ወቅታዊ የሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ አስፈላጊ ነው ብሏል።
በቅርቡ የተፈጸመውን የመተከል ዞን ጥቃት፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እያካሄዳቸው ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶችን እና በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው አመራሮች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሆነም ከባልደራስ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የታሰበው ጥር 9 ቀን እንደሆነ ከወዲሁ ቢነገርም፤ ሰልፉ እንዲካሄድ በመንግሥት ፈቃድ ቢሰጥ እንኳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ይጠበቃል። ከጥር 10 የከተራ በዓል አንስቶ እስከ ጥቅምት 12 ለሚከበረው የጥምቀት በዓል የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌደራል ፖሊስ አባላት ሙሉ በሙሉ በፀጥታ ሥራ ላይ እንዲሠማሩ የሚደረግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጥያቄው ውድቅ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው። ቀኑ የተመረጠበት ምክንያት አልተገለፀም።

LEAVE A REPLY