ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በመተከል ዞን ከተከሰተው የፀጥታ ጥቃት ላይ እጃቸው አለበት ተብለው የሚጠረጠሩት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን አስተዳዳሪ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰማ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በትናንትናው እለት እንደሆነ የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሓላፊ ገልጸዋል።
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት በቁጥጥር ስር የዋሉት በተደጋጋሚ የታዩ የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ባለመፍታት እና ሓላፊነት ባለመወጣት ተጠርጥረው እንደሆነ ቢነገርም፤ ከተለያዮ ወገኖች በንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት እጃቸው አለበት የሚሉ ጥቆማዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።