በኦሮሚያ የሚገነባው “ገዳ ልዮ የኢኮኖሚ ዞን” ፕሮጀክት ለሠባት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል...

በኦሮሚያ የሚገነባው “ገዳ ልዮ የኢኮኖሚ ዞን” ፕሮጀክት ለሠባት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን” ፕሮጀክት ለ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥርና 12 ሺህ 500 በላይ የውጭ ባለሃብቶች ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ ተገለጸ።

መልክዓምድራዊ አቀማመጥን በመጠቀም ኢትዮጵያ እና ምስራቅ አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት በውስጡም ዐሥር የውጭ ገበያ የሚፈጥሩ እና ሥድሥት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት የሚሠሩ የማምረቻ ተቋማት እንዳሉት የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ አስረድተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሐሳብ አመንጪነት የሚሠራው ፕሮጀክት፤ የኢኮኖሚ ዞኑ በአዳማ እና ሞጆ አካባቢ በሚገኝ 23 ሺኅ 656 ነጥብ 51 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍና በአካባቢው ለሚገኙ 33ሺኅ ሰዎች የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ ህግ መፅደቁን ከሥራ አስኪያጁ መግለጫ መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY