ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የደራሲ፣ አዘጋጅ፣ ተዋናይት እና ተራኪ ባዩሽ አለማየሁ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ።
በሀገር ፍቅር ቴአትር ከሃያ አመት በላይ ያገለገለችው እና በመድረክ የትወና ብቃቷ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችው የአርቲስት ባዩሽ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወዳጅ ፣ ዘመዶቿ እና አርቲስቶች እንዲሁም አድናቂዎቿ በተገኙበት በቅድስት ሥላሤ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ፎርፌ፣ ገጽ ሁለት እና ረመጥ የተሰኙ የመድረክ ቴአትሮችን የጻፈችው አርቲስት ባዮሽ አለማየሁ የታዋቂው ደራሲና ተርጓሚ መስፍን አለማየሁ ልጅ ስትሆን፤ ከሁለት ዐሥርት አመታት በላይ በዘለቀው የትወና ሕይወቷ የቬኑሱ ነጋዴ፣ የስለት ልጅ፣ ሰማያዊ ዐይን፣ ትዳር ሲታጠን፣ ነቃሽ እና ሰዐት እላፊ የተሰኙት ቴአትሮች ከበርካታ የመድረክ ሥራዎቿ መካከል ለአብነት ይጠቀሳሉ።