ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙሌትና ውኃ አለቃቀቅ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ግብፅና ሱዳን መካከል ዛሬ እንደገና እንደሚጀመር የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
በደቡብ አፍሪካ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት እና የቢሮው ሊቀ መንበር የውጪ ግኑኝነትና ትብብር ሚኒስትር የተጠራው ስብሰባ የሦስቱን ሀገሮች በአጠቃላይ 6 የውጪ እና የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ይይዛል ነው የተባለው።
ታዛቢዎችና በሕብረቱ የተሰየሙ ኤክስፐርቶችም በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ ከወጣው መግለጫ መስማት ችለናል።