በመተከሉ ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 17 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በመተከሉ ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 17 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ከተባሉት ታጣቂዎች መካከል 17ቱ በሕዝቡ ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀረ ሽምቅና ልዩ ጥበቃ አድማ ብተና መምሪያ ገለጸ።

እነዚህ ታጣቂዎች ከለውጡ በኋላ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለእኩይ ዓላማ የተሰለፉ እና በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድሉ፤ ሲያፈናቀሉና ንብረት ሲዘርፉ የቆዮ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ለጥቃቱ በክልሉ ከህወሓት የጥፋት ቡድን ጋር የተመሳጠሩ አመራሮች ሚና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ ከሰሞኑ በመተከል ዞን ቡለንና በቆጂ ወረዳዎች በዜጎች ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያም በእነዚሁ አካላት የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ ተነግሯል።
ግብረ ሀይሉ ባደረገው ዘመቻ ከዳንጉር፣ ድባጤ፣ ቡለንና ማንዱራ ወረዳዎች ጥቃት ካደረሱት ታጣቂዎች መካከል በአካባቢው ሕዝብ ጥቆማና ትብብር 17 በቁጥጥር ሥር ማዋሉንም ጠቁሞ፤ ከታጣቂዎቹ ጋር ከ29 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የባለ 5፣ 10፣ 50፣ 100 የሞባይል ካርዶች፣ 290 ቀስቶች፣ መድኃኒቶችና ሌሎች ቁሳቁሶችም መያዛቸውን አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY