ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፊዚካል አፈጻጸሙ 70 በመቶ መድረሱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የፓርኩ ግንባታ ከ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ በሲሲሲሲ በተሰኘው የቻይና ተቋራጭ ሥራው እየተከናወነ እንደሚገኝ ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኩ በመንግሥት እየለሙ ከሚገኙ ፓርኮች 13ኛው ቢሆንም፤ በቅርቡ ፌደራል መንግሥቱ በሀገሪቱ የተለያዮ ክልሎች የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለግል ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ሊሸጡ እንደሚችሉ መጠቆሙ አይዘነጋም።
በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ የሚገኘው ይህ ፓርክ ጠቅላላ ስፋቱ 2 ሺኅ ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ፓርኩ ሲጠናቀቅ የሎጅስቲክ ፓርክ በመሆን ሌሎቹን ፓርኮች ያስተሳስራል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።