ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ግዙፍ የወርቅ ማቅለጫ ፋብሪካ በቀጣዮቹ ወራት ሊገነባ መታሰቡ ተሰማ።
በዋና መዲናዋ የሚገነባው ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ማቅለጫ እንደሚገነባ ያረጋገጠው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ነው።
ይህንን የወርቅ ማቅለጫ መገንባት እንደ ኢትዮጵያ ላለች የወርቅ ማዕድን ላላት ሀገር ጠቀሜታው የጎላ ነው ያሉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ ማቅለጫው ኢንተርናሽናል ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ በመንግሥትና ባለሀብቶች እንደሚገነባ ገልጸዋል።
ፋብሪካው ከተገነባ በኋላ ሀገሪቱ የሚኖራትን የተጣራ የወርቅ ክምችት ሀብት መጠን ከፍ ያደርገዋል ተብሎለታል።