ግብፅ በአፍሪካ ሕብረት የተሰየሙ ባለሙያዎች ያቀረቡትን ሰነድ አልቀበልም ማለቷ ተሰማ

ግብፅ በአፍሪካ ሕብረት የተሰየሙ ባለሙያዎች ያቀረቡትን ሰነድ አልቀበልም ማለቷ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዳግም ትናንት በተጀመረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት ላይ ግብጽ በአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የተሰየሙ ባለሙያዎች ያቀረቡትን ረቂቅ ሰነድ አልቀበልም ማለቷ ተሰማ።

የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ ለአንድ ወር ያህል ተቋርጦ ቆይቶ በተጀመረው ውይይት ላይ በባለሙያዎች የቀረበውን ረቂቅ ሰነድ ኢትዮጵያና ሱዳን በአዎንታዊ መልኩ ተቀብለውታል።
በሦስቱ ሀገራት ስብሰባ የውጭ ጉዳይና የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸው እና የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ባቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አድርገው ነበር።
ኢትዮጵያ የቀረበውን ሰነድ እንደምትቀበለውና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን አሳውቃለች ያለው መግለጫ፤ ሱዳንም ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ  እንደሆነ በመግለጽ ድርድሩን መቀጠል ፍላጎት እንዳላት ብታሳውቅም፣ ግብፅ ግብፅ ግን ሰነዱን ጨርሶ እንደማትቀበለው ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY