ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ቀደም ሲል የተፈጸመው ውል ውድቅ እንዲሆን የተደረገበት ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይንን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
100 ሜጋዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ በአዳማ እና አሰላ መካከል የሚገኝ ሲሆን፤ በተፈጸመው ስምምነት መሠረት ሰይሜንስ ጋሜሳ ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ኤስጂ 3 ነጥብ 4 -132 የነፋስ ተርባይኖችን ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ ያቀርባል።
ለነፋሰ ሀይል ማመንጫው ኢትዮጵያ እና የዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል። ከዚህ ውስጥ 94 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮው የባንኩ ግሩፕ በድጋፍ መልክ የሚሰጠው እንደሆነም ተገልጿል።