ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኦነግ ሸኔ ጦር በነፃነትና በብዛት ይንቀሳቀስበታል በሚባለው በምስራቅ ወለጋ ያሉ ዜጎች መንግሥት ከለላ ሊያደርግልን ይገባል አሉ።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በሚገኑት በሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ሊመ ገሊላና ኪረሙ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች መንግሥት ደህንነታችንን ከማስጠበቅ ይልቅ ለሚደርስብን ችግር ተባባሪ ሆኖብናል በማለት ነው ምሬታቸውን የገለጹት።
በአካባቢው በተደጋጋሚ በሚደርሱ የጸጥታ ችግሮች እየተንገላታን ነው ያሉት እነዚህ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ችግር የማያጣቸው ሆሮ ጉድሩና ሊሙ ገሊላ ውስጥ ያሉ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የችግሩ ተባባሪ በመሆን ችግሩ መፍትሔ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆነውብናል ሲሉም ይከሳሉ።
በአካባቢው የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ለበላይ አካላት መረጃ መስጠታቸው እየጎዳን ነው ያሉት ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
በተያያዘም የምዕራብ ወለጋ ነዋሪዎች ዛሬ የኦነግ ሺኔን በመቃወም ሰለማዊ ሰለፍ ያደረጉ ሲሆን ኦነግ በአከባቢው እያደረሰ ያለውን ዘገነኘ ጥፋት አውግዘዋል።