በአልነጃሺ መስጊድ እና በአማኑኤል ምንጉዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት መድረሱን መንግሥት አረጋገጠ

በአልነጃሺ መስጊድ እና በአማኑኤል ምንጉዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት መድረሱን መንግሥት አረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ፀጥታ የራቃት በምትመስለው ትግራይ ክልል በሚገኘው አል ነጃሺ መስጊድ ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ መንግሥት መግለጫ ሰጠ።

ከውቅሮ ከተማ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘው ጥንታዊው የአል ነጃሺ መስጅድ እና በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት መድረሱን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው።
 አል ነጃሺ መስጂድ እና በአማኑኤል ምንጉዋ ቤተክርስትያን ላይ ጉዳት ደርሷል ያሉት የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ በሁለቱም የእምነት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት፤ እንዲሁም በውስጣቸው የነበሩ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ የሚያጣራና የሚመረምር ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚላክ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ጄይላን ከድር በመስጂዱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት በቂ መረጃ እንዳልደረሳቸው ጠቁመው ከሁለት ቀናት በኋላ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ይፋ እንደሚቋቋም ከወዲሁ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY