ምዕመኑ የገናን በዓል የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ እንዲያከብር ብፁዕ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ

ምዕመኑ የገናን በዓል የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ እንዲያከብር ብፁዕ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ህዝበ ክርስቲያኑ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን ሲያከብር የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ የተራቡትንና የተጠሙትን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም የታረዙን በማልበስ ሊያከብር እንደሚገባ የኃይማኖት አባቶች መከሩ።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቴክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስ፤ “ከጥንት ጀምሮ የነገረንን ተስፋውን ለመፈጸም በዚህ ዓለም የተወለደው የተስፋ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገራት፣ በየማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና በተለያዩ ቦታዎች በዓሉን ለሚያከብሩት እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ” ብለዋል፡፡
ምዕመኑ የክርስቶስን ልደት በዓል ስያከብር ለእግዚአብሔር ክብር በመቆም፣ ለሰው ልጅ ሰላምን ለመስጠትና ለመቀበል በመዘጋጀት ሊሆን እንደሚገባም ምክር ለግሰዋል።

LEAVE A REPLY