በነዳጅ እጥረት ምክንያት በመቀሌ ተንቀሳቅሰው ለመሥራት እንደተቸገሩ አሽከርካሪዎች ገለጹ

በነዳጅ እጥረት ምክንያት በመቀሌ ተንቀሳቅሰው ለመሥራት እንደተቸገሩ አሽከርካሪዎች ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በመቀሌ ከተማ ባጋጠማቸው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ተንቀሳቅሰው ለመስራት መቸገራቸውን አሽከርካሪዎች ገለጹ።

ጉዳዮን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ከጅቡቲ እየመጡ በመሆኑ ችግሩ በቅርቡ ይቃለላል ብሏል።
የነዳጅ እጥረት ለመንቀሳቀስ ፈተና ሆኖብናል ያሉት አሽከርካሪዎች፤ በተለይም የባለ ሦስት እግር ባጃጅ እና የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጦት የተነሳ ከሚሠሩበት ጊዜ የማይሠሩበት እንደሚበልጥ አስረድተዋል።
በነዳጅ ማደያዎች በ21 ብር የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን በጥቁር ገበያ እስከ 100 ብር እየተሸጠ ነው ያሉት አሽከርካሪዎቹ፤ የከተማ ታክሲ አሽከርካሪዎችንም በተመሳሳይ የነዳጅ እጥረቱ ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ያደረጋቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY