አዲስ ዓለም ባሌማ ላይ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናትን ፈቀደ

አዲስ ዓለም ባሌማ ላይ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናትን ፈቀደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና በትግራይ ክልል በሚገኘው ሰሜን ዕዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩት አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ ዳግመኛ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት አምባሳደር አዲስ ዓለም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አጀንዳዎችን አስቀድሞ በማውጣት ለዶ/ር ደብረፂዮን አሳልፎ በመስጠት ፣ እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥር ቅስቀሳ አካሂደዋል በሚል  ተከሰው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
ከዚህ በተጨማሪም ግለሰቡ በትግራይ ክልል በፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ተባባሪ እንደነበርና ዲያስፖራዎች ለህወሓት ቡድን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲቀሰቅሱ እንደነበረ የሚያሳይ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች አሰባስቤያሁ ያለው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራዎች አስራ አራት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎታል።

LEAVE A REPLY