ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ተከትሎ የመንጋ ቡድን አባላት ባነሱት ኹከት እና በደረሰው ጥቃት ከፍተኛ ንብረት የወደመባቸው የሻሸመኔ ነዋሪዎች የግብር እፎይታ እንዳልተሰጣቸው ገለጹ።
ከዛ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ኹከቶች እና በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠሩ ግጭቶች አማካኝነት ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች የግብር እፎይታ ይሰጣቸዋል ተብለው ቃል ተገብቶላቸው የነበረ ቢሆንም በተግባር ግን እየሆነ ያለው ግን ፈጽሞ ከዚህ የተለየ እንደሆነ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት “ግብር ካልከፈላችሁ ንግድ ፍቃድ ማደስም ሆነ ክሊራንስ መውሰድ አትችሉም እየተባልን ነው” ያሉት በሻሸመኔ የሚገኙ እና ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች መንግሥት በይፋ ቃል የገባውን የእፎይታ ጊዜ በውስጥ አሠራር ሽሮታል ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።