ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች ሲጫወቱ ለነበሩ ተጫዋቾች የፈቀደው ልዩ የዝውውር ጊዜ እስከ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታወቀ።
የተጫዋቾች ዝውውሩ በክልሉ በነበረው ሰላም የማስከበር ዘመቻ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ፤ ከታኅሣሥ 26 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተጨማሪ ለአምስት የሥራ ቀናት የተፈቀደ ነበር።
የማራዘሚያ ቀናት መጨመር ያስፈለገው ከላይ ከተገለጸው ምክንያት በተጨማሪ ታህሣሥ 29 ቀን የገና በዓል ምክንያት እንደሆነም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።