ቦይንግ ለተመሠረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ብር ሊከፍል ነው

ቦይንግ ለተመሠረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ብር ሊከፍል ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ግዙፉ ቦይንግ  ካምፓኒ ስለ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል መስማማቱ ተነገረ።

ኩባንያው “ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን” አስቀድሟል ያለው የአሜሪካ የፍትህ ተቋም፤ ቦይንግ ለመክፈል ከተስማማው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ በአውሮፕላኑ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ የሚከፋፈል እንደሆነና ይህ ስምምነት ኩባንያው ያለበት ጉድለት ምን ያህል እንደሆነም ጭምር አመላካች ነው ብሏል።
 “ወደ እዚህ ስምምነት መግባታችን ትክክለኛው ነገር እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፤ ይህም ከእሴቶቻችን እና ከሚጠበቅብን ምን ያህል ወደ ኋላ መቅረታችንን ያሳያል። ስምምነት ሁላችንንም የሚያስታውሰን ለግልጽነት የገባነው ግዴታ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፤ እንዲሁም አንዳችንም እንኳን እርሱን ሳናሟላ ብንቀር መዘዙ የከፋ መሆኑን ነው።”
ያሉት የቦይንግ የሥራ ሒደት ሓላፊም ካምፓኒው ከፍተኛ ስህተት መፈጸሙን አምነዋል።

LEAVE A REPLY