አቦይ ስብሓት ነጋ ከባለቤቱ ጋር ጢሻ ውስጥ ተደብቆ ተያዘ፤ ጠባቂዎቹ ሙሉ ለሙሉ...

አቦይ ስብሓት ነጋ ከባለቤቱ ጋር ጢሻ ውስጥ ተደብቆ ተያዘ፤ ጠባቂዎቹ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 30 ዓመታት ዋነኛ የጥፋት መሀንዲስ የነበረው የህወሓቱ አንጋፋ መሪ ሰብሐት ነጋ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፤ ስብሓት ነጋ ለሰው ልጅ በእጅጉ አስቸጋሪ በሆነ ሰርጥ ውስጥ ተደብቆ በመከላከያ ሠራዊት መያዙን ይፋ አድርገዋል።
የጥፋት ቡድኑ አባላት ሽማግሌውና የጥፋት ስትራጂስቱን በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበር ያስረዱት ጀነራሉ፤ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ፣ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር አውለውታል ብለዋል።
ሌሎች ከሃዲ የጁንታው ቡድን አመራሮችም ከጁንታው መሪ ስብሃት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መግለጫው ያሳያል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሠረት በቁጥጥር ሥር የዋሉት፦
1.  የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ
2.  ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች
3.  ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ
4.  ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዳ
5.  አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ሃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን
6.  የሜጀር ጀነራል ኃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች፣ በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ መሆናቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY