ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መገደላቸው እና መያዛቸው ተነገረ

ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መገደላቸው እና መያዛቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ የጁንታው ጉጀሌ ከፍተኛ አመራር ከነበሩት ውስጥ አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸውና ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ አራት ሰዎች መገደላቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

ከሁለት ወር በፊት “የሰሜን ዕዝን በ45 ደቂቃ ውስጥ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም ከጥቅም ውጭ አድርገነዋል” ያሉት አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸውን ጨምሮ እነዚህ 4 ከፍተኛ የህወሓት ቡድን አመራሮች ከነአጃቢዎቻቸውና ጠባቂዎቻቸው እንደተገደሉና፤ ሌሎች 9  ከፍተኛ አመራሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከመግለጫው መረዳት ችለናል።
የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ፤ ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ እና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስረድተዋል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተገደሉ እና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን በተመለከተ ያወጣውን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
የተገደሉ፦
1.  አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው፣
2. አቶ ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ፣
3. አበበ ገብረመድህን የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበሩ፣
4. ዳንኤል አሰፋ (የጌታቸው አሰፋ ወንድም) የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሓላፊ ነበሩ
 በቁጥጥር ስር የዋሉ፦
1. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበሩ፣
2.  ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩ፣
3.  አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፣
4.  አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
5.  አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣
6.  አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበሩና የቡድኑ ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀሉ፣
7.  አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበሩ፣
8.  ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበሩ እንዲሁም
9.  አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ሥራ ሂደት ሓላፊ የነበሩ ናቸው

LEAVE A REPLY