በትግራይ ሁሉም ቦታዎች አስቸኳይ የእርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች አውሮፓ ሕብረት ጠየቀ

በትግራይ ሁሉም ቦታዎች አስቸኳይ የእርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች አውሮፓ ሕብረት ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ሓላፊ ጠየቁ።

የእርዳታ ድርጅቶች ከጥቂት ቀናት ወዲህ የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች አንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ይህ ከህወሓት ጋር ውጊያዎች የተካሄዱባቸውን ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች የሚያካትት አይደለም ነው የተባለው።
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሓላፊው ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር መመቻቸት እንዳለበት ጠቁመው፤ ይህ ጥያቄ ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ሳይሆን በዓለም ዐቀፍ ሕግ መሰረት መፈጸም ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲሉም አሳስበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉና ኤርትራዊያን ስደተኞችን የሚያስጠልሉ ሁለት የስደተኛ ካምፖችን ለመጎብኘት እንዳልቻለ ማመልከቱ ይታወሳል።
የስደተኛ ካምፖቹን የሚያሳዩ የሳተላይት ምሰሎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም ህንጻን ጨምሮ በካምፖቹ ውስጥ የሚገኙ ቤቶች መውደማቸውን አመልክተዋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY