ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ ከጂቡቲ መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ዘካሪያ ሼህ ኢብራሂም የሃገሪቱን የመጨረሻ ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን መሸለማቸው ተነገረ።
በኒሻን ማልበስ ሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የሰላም ማስከበር ማዕከል ሓላፊ ሌተናል ጀነራል ደስታ አብቼ my፤ ጀነራል ብርሃኑ ከጂቡቲ መንግሥት የተበረከተላቸው ኒሻን በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተፈቅዶ የተሰጣቸውና የመጨረሻ ከፍተኛ ደረጃ ኒሻን መሆኑን ገልጸዋል።
ጀነራል ብርሃኑ በወታደራዊ የአመራር ክህሎታቸው ባሳዩት ድንቅ የመሪነት ብቃት በሀገሪቱ አጋጥሞ የነበረው አደጋ እንዲቀለበስ በማድረግና ህግ የማስከበሩን ተግባር መከላከያ ሠራዊት በአኩሪ ጀግንነት እንዲፈፅም የመሪነት ሚናቸውን በመወጣት ፣ ኢትዮጵያን እና የአካባቢው ሀገራት ከተጋረጠባቸው ከፍተኛ አደጋ በማዳናቸው እንደተበረከተላቸው ተሰምቷል።