በምዕራብ ወለጋ ስምንት የኦነግ ሸኔ አባላት መገደላቸው ተሰማ

በምዕራብ ወለጋ ስምንት የኦነግ ሸኔ አባላት መገደላቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ስምንት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ።

ከዚህ በተጨማሪ ሥድሥት የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ከሰማኒያ በላይ ደጋፊዎቻቸው መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ለሁለት ወራት በዞኑ በተደረገው የሕግ የበላይነት የማስከበር ዘመቻ 265 የኦነግ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ እና የኦነግ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበረው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY