በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን የሆኑ 12 የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎች የወሰን ጥያቄ አለባቸው

በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን የሆኑ 12 የጥምቀት ማክበሪያ ቦታዎች የወሰን ጥያቄ አለባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ የጥምቀት በዓል የሚከበርባቸው አብዛኞቹ ስፍራዎች የወሰን ጥያቄ ያለባቸው መሆኑ ተነገረ።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይዞታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሆኑ 12 የጥምቀት በዓል ይከበርባቸው የነበሩ ቦታዎች ላይ የወሰን ማስከበር ጥያቄ እንዳለባቸው የገለጸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው።
በከተማዋ ከታላቁ የጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ 20 ስፍራዎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ንበረት መሆናቸው ቢታወቁም በትክክል ሕጋዊ እውቅና ያገኙት ስምንቱ ብቻ እንደሆኑና ቀሪዎቹ ቦታዎች ከተለያዮ አካላት ጋር የተያያዘ የወሰን ጥያቄ እንዳለባቸው ተሰምቷል።
እነዚህ ቦታዎች ባለፉት ዓመታት ጥምቀት ሲከበርባቸው የነበሩ ሲሆን፤ ከይዞታዎቹ መካከል ሕጋዊ ካርታ ያላቸው እና ካርታ ሊሠራላቸው በሂደት ላይ የነበሩ እንደሚገኙበትም ሀገረ ስብከቱ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY