በአዳማ ከተማ ነጋዴዎች ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተፈጸመብን ነው አሉ

በአዳማ ከተማ ነጋዴዎች ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እየተፈጸመብን ነው አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ በአዳማ ከተማ የሚገኙ በተለያየ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ የተመረጡ ነጋዴዎች ከቫት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የገንዘብ ጥቃት እየተቀጣን ነው አሉ።

“ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እየተጠቀማችሁ አይደለም” በሚል ያለ ምንም ማስረጃ ከ50 ሺኅ ብር ጀምሮ እስከ 100 ሺኅ ብር ድረስ ቅጣት እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ቅሬታቸውን ያሰሙት ነጋዴዎች ቅጣቱን መክፈል እንዳለባቸው የሚያሳይ የቅጣት ደብዳቤ እየተሰጣቸው እንደሆነ ከመናገራቸው ባሻገር፤ “ከህግ አግባብ ውጪ እጅ ከፍንጅም ሆነ ያለ ቫት ስንሸጥ ሳንገኝ ፣ በየሱቃችን እየመጡ ቫት እንደማትጠቀሙ ታውቋል በሚል ከ 50 ሺሕ ብር ጀምሮ 100 ሺሕ ብር ድረስ ቅጣት ክፈሉ” በሚል አስገዳጅ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY