የኦሮሚያ ብልፅግና በቅርስነት የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ አፈረሰ

የኦሮሚያ ብልፅግና በቅርስነት የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ አፈረሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ የደጅ አዝማጅ አስፋው ከበደ መኖሪያ ቅርስ እንደሆነ እየታወቀ የኦሮሚያ ብልፅግና ቤቱን እንዳፈረሰው ተሰማ።

የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን ከፍተኛ ሓላፊዎች ቅርስ ፈረሳውን ለማስቆም ወደ መኖሪያ ግቢው ቢደርሱ ወታደሮች እንዳይገቡ እንደከለከሏቸው እና መኖሪያውንም እንዳልነበር አድርገው ማፈራረሳቸውንም ይፋ አድርገዋል።
ደጃዝማች አስፋው ከበደ ትልቅ ባለአባት የነበሩ፣ የገነተ ልዑል  የንጉሠ ነግሥቱ ቤተመንግሥት በነበረበት ጊዜ የግቢ ሚኒስቴር በመሆን ያገለገሉ ናቸው።
ለቅርበቱ ተብሎ በእዛን ወቅት የእርሳቸው መኖሪያ ቤት መነን ት/ቤት ፊት ለፊት ተሠርቶ በቅርስነትም ተመዝግቦ ነበር። ነገር ግን ይህ ቅርስ ሆን ተብሎ ሙሉ ለሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል።
ይህ ታሪካዊ መኖሪያ ሲፈርስ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ራሱ የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን ፈጽሞ እንደማያውቅ ነው የተነገረው።
ባለፈው አርብ ጣሪያው ሲፈርስ ማን አፍርሱ ብሎ እንዳዘዘ ማወቅ አልቻልንም ሲሉ ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት የቅርስና ጥበቃ ባለሥልጣን ም/ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ “ቅዳሜ እለት ወደ ውስጥ ዘልቀን በመግባት ለማስቆም ስንሞክር በወታደሮች እንዳንገባ ተከልክለን ተመልሰናል” በማለት ተናግረዋል።
ቦታውን በባለቤትነት ለመያዝ የተዘጋጀው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ እንደሆነና ስፍራውን ለኦሮሚያ ፖሊስ ልዮ ኃይል ካምፕ ግንባታ እፈልገዋለሁ ማለቱን የጠቆሙት ፕሮፌሰር አበባው፤ በአሁን ሰዐት ሙሉ ለሙሉ ፍርስራሹን አውጥተው በመጣል ታሪካዊውን ቅርስ “ካርታ አዌይ” እንዳደረጉት አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY