ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃዬ፣ አስመላሽ ወ/ ሥላሤን ጨምሮ የጁንታው አመራሮች ተደመሰሱ

ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃዬ፣ አስመላሽ ወ/ ሥላሤን ጨምሮ የጁንታው አመራሮች ተደመሰሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ የከሀዲው የህወሓት ዋነኛ መሪ የሆኑት  አቶ ስዩም መስፍን ፣አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ (ዐይነ ስውሩ)፣ አቶ አባይ ፀሐዬን ጨምሮ በርካታ የጁንታው አመራሮች ተደመሰሱ።

የመከላከያ ሠራዊት ሀይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን አረጋግጠዋል።
የጁንታው ቡድን አመራሮች ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ በመቀሌ በተካሄደው ዘመቻና ድምሰሳ ወቅት በ48 ሰዐት እጅ እንዲሰጡ ቢለመኑም፣ በማናለብኝነትና ትዕቢተኝነት እምቢ በማለት ወደ ጫካ መግባታቸውን ብ/ ጀነራል ተስፋዬ አስታውሰዋል። ጀነራሉ በድጋሚም የአገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሽማግሌ ጭምር በመላክ እጅ እንዲሰጡ፣ ትጥቅ እንዲፈቱና ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ቢያስጠይቅም አሻፈረኝ በማለት የያዙትን የጥበቃ ሀይል በመተማመን፣ እንዲሁም ተመልሰን እንነሳለን በሚል የድሮ ብሂል ተሳስተው ያለ እድሜያቸው በዱር በገደሉ ተሸሽገዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

ስዩም መስፍንን እና አባይ ፀሐዬን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ

በውጊያ ከጥበቃዎቻቸው ጋር አብረው የተደመሰሱ የጁንታው አመራሮች፣

1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ባስተላለፉት መልዕክት፣ አሁንም በየዋሻው የተደበቁ የጁንታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።“ትርጉም ለሌለው ጁንታ ጠባቂ በመሆን ውድ ህይወታቸውን አትገብሩ፣ ከቻላችሁ ይዛችኋቸው፣ ካልቻላችሁ በሰላም ለሰራዊቱ እጅ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ጁንታው ተመልሶ ይመጣል በሚል ያላቸው ግምት የተሳሳተና የጁንታው ቡድን ዘመን ያከተመ መሆኑን አውቀው፣ ከሀገራቸውና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ ሽግግር መንግስት ጎን በመሆን ትግራይን እንዲያደራጁ፣ እንዲያለሙና መላው ህዝብም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረበቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY