በመተከሉ ጥቃት የ2 አመት ሕጻንን ጨምሮ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰማኮ ይፋ...

በመተከሉ ጥቃት የ2 አመት ሕጻንን ጨምሮ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ኢሰማኮ ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡  ከበቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በታጣቂዎች የተገደሉት ንጹሐን ዜጎች ቁጥር ከሰማኒያ በላይ መሆኑን እንዳረጋገጠ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ።

በመተከል ዞን፣ በደባተ ወረዳ፣ ዳለቺ በምትባል ከተማ ጥቃቱ መፈጸሙን የተናገሩት የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ እና ቃል አቀባይ አቶ አሮን ማሾ፤ ለኮሚሽኑ በደረሰው መረጃ መሰረት ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ከ80 በላይ እንደሚሆኑ እና እድሜያቸውም ከ2 አመት ሕጻን እስከ 45 አመት ጎልማሳ እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
በስፍራው ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ግድያዎች መድረሱን ያስታወሱት አቶ አሮን ማሾ፤ በፌደራልና በክልሉ መንግሥት እየተወሰደ ያለው እርምጃ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አሳስበዋል።
ከትናንት በስቲያ (ሰኞ ዕለት) ብቻ በጉባ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸውን የጠቆመው በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በሰሞኑ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ግምቱን ከማስቀመጡ ባሻገር፤ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ በእጅጉ ያሳሰበው መሆኑን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY