ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሰሞኑን የድንበር ወረራ ያካሄደችው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ምሥራቃዊው የአል-ቀዳሪፍ ግዛት ላይ ማንኛውንም የአየር በረራ እንዳይካሄድ ማገዷ ተሰማ።
በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል የአል ቀዳሪፍና የአል ፋሽጋ አየር ክልል ላይ ማንኛውም በረራ እንዳይካሄድ ውሳኔ ያሳለፈው የሱዳን ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ነው።
የአገሪቱ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ኃላፊ ኢብራሂም አድላን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ረቡዕ ዕለት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሱዳንን አየር ክልልን ጥሶ ገብቷል በሚል አገራቸው ከከሰሰች በኋላ እንደሆነ እየተነገረ ነው።