የትግራይ ሰሞነኛ ውጥረት የውጭ ምንዛሬን ዋጋ በእጅጉ ሰቅሎታል ተባለ

የትግራይ ሰሞነኛ ውጥረት የውጭ ምንዛሬን ዋጋ በእጅጉ ሰቅሎታል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ የተከሰተውን ሰሞነኛ ችግር ተከትሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነት በእጅጉ መጨመሩንና የውጭ ምንዛሪም ጣራ መንካቱ ተነገረ።

በኢትዮጵያ ይፋዊ የባንክ ግብይት መሰረት አሁን አንድ ዶላር 39.7 (40 ብር) ቢመነዘርም በጥቁር ገበያ ደግሞ የአንድ ምንዛሬ ዋጋ 55 ብር መድረሱን ቢቢሲ አደረግኹት ያለውን ቅኝት ተከትሎ መረጃውን ይፋ አድርጓል።
በተለይም ሀገሪቷ የይፋዊ እና በጥቁር ገበያ የምንዛሪ መሀል ያለውን ተመንን ዋጋ ለማቀራረብ እየሠራችበት ባለችበት ወቅት በጥቁር ገበያና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለው ልዩነት አስራ ሥድሥት ብር ገደማ መሆኑ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን ስጋት ላይ ጥሏል ነው የተባለው።
 በትግራይ ክልል ባለው ወታደራዊ ግጭት፣ አገሪቷ ባጋጠማት አለመረጋጋት ምክንያት የጥቁር ገበያው ዋጋ በእጅጉ መናሩን የጠቆሙት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች፤  የብር ከዶላርም ሆነ ከሌሎች የመገበያያ ገንዘቦች አንፃር መድከም በዓመታት ውስጥ የታየ እንደሆነም አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ሚሊኒየም ዋዜማ የአንድ ዶላር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንዛሪ 8. 37 መሆኑንም ለእዚህ ትንታኔ ማስተማመኛ እንዲሆኑ በዋቢነት ያቀርባሉ።

LEAVE A REPLY