የጁንታውን ውድቀት ለማመን የተቸገረ ብዙ የትግራይ ሰው መኖሩን ነቢዮ ስሁል ሚካኤል ገለጹ

የጁንታውን ውድቀት ለማመን የተቸገረ ብዙ የትግራይ ሰው መኖሩን ነቢዮ ስሁል ሚካኤል ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የጁንታው አመራሮች እና ስትራቴጂስቶች መያዝ ለትግራይ ህዝብ ትልቅ የነፃነት ተስፋ ያነገሰ መሆኑን የትግራይ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ገለጹ።

የትግራይ ህዝብ ለዓመታት ስርዓቱ የሚገረሰስ በማይመስል ደረጃ ትልቅ ፕሮፖጋንዳ እየተነዛበትና አፈና እየተጫነበት መኖሩን ኖሯል ያሉት ወጣቱ የብልጽግና አመራር፤ የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስቱ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ወልዱ እና ዶክተር አብረሀም ተከስተን ጨምሮ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች መያዛቸውን ተከትሎ፤ አሁን ላይ የትግራይ ህዝብ ስሜት ደስታና ተስፋ የነገሰበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
“ከነበረው ፕሮፖጋንዳ አንጻር ነገሮችን ለማመን የተቸገረ ሰው ብዛት ቀላል ባይሆንም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም የጁንታው አመራሮች መያዝ ለውጡን በሙሉ ልብ ወደ መቀበሉ እየሄደ እንዳለ የሚያመላክቱ ማሳያዎች እየበዙ መጥተዋል” በማለት የተናገሩት የታሪክ መምህር፣ ደራሲ እና የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራር አቶ ነቢዮ ስሁል ሚካኤል፤ የህወሓት አጥፊ ቡድን መሪዎች መያዝ መጀመራቸው ብዙ መልዕክት አለው ብለዋል።
 በዋነኛነት ከሕግ አንፃር ሊጠቀስ የሚችለው ማንኛውም እና በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ ሰው ህግ ቢጥስ እና ቢያጠፋ በህግ ፊት የሚቀርብ እና ጊዜ ጠብቆ ተጠያቂነቱ የማይቀር መሆኑን የሚያሳይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ያሉት አመራሩ፤ “ለትግራይ ሕዝብ በተለይ ለወጣቱ የለውጥ ምዕራፍ ወለል ብሎ መከፈት መጀመሩን ያበሰረ  ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉ አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY