አባይ ወልዱ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በአእምሮ ጭንቀት ሕመም ጦር ኃይሎች ሆስፒታል...

አባይ ወልዱ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በአእምሮ ጭንቀት ሕመም ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ትግራይ ውስጥ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ የተያዙት የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አባይ ወልዱ በጠና ታመው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል መተኛታቸው ተሰማ።

ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደነገሩን ከሆነ ሲያዙ በድንጋጤ የለበሱት ልብስ ላይ የተዝረከረኩት አቶ አባይ ወልዱ አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት ጤነኛ የነበሩ ቢሆንም፤ የወደ ፊቱ ማረፊያቸውን ከተመለከቱ በኋላ በእጅጉ መታመማቸውን ገልጸዋል።
አቶ አባይ ወልዱ በአሁኑ ሰዐት በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ውስጥ በልዮ ክፍል ሕክምናቸውን እንዲከታተሉ የተደረገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ትናንት በነበረው ችሎት ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።
 በተመሳሳይ ትግራይ ላይ የተያዘው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ሓላፊ የነበሩት ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ  ሕክምና ላይ በመሆናቸው በችሎቱ ሳይገኙ ቀርተዋል።
በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተሰጣቸውን  ከፍተኛ ሥልጣን ገፍተው ወደመቀሌ ሄደው የመሸጉት የጁንታው አባል ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ለአእምሮ ጭንቀት እና ሕመም መዳረጋቸውን የጠቆሙ የኢትዮጵያ ነገ ታማኝ ምንጮች፤ ሁለቱም ግለሰቦች በቂ ሕክምና እንዲያገኙ በመንግሥት በኩል ተገቢው ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY