ምርጫ ቦርድ የክልል መንግሥታትን ትብብር ጠየቀ

ምርጫ ቦርድ የክልል መንግሥታትን ትብብር ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ሥድሥተኛውን ሀገራዊ ምርጫ እያዘጋጀ የሚገኘው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጸጥታን ማረጋገጥ እንዲሁም የምርጫ ክልል እና የዞን ቢሮዎችን ከፍቶ ወደ ሥራ ከመግባት ጋር በተያያዘ የተለያዮ ትብብሮችን ለክልል መንግሥታት አቅርቧል።

በተለያዩ ወቅቶች ከክልል መስተዳድር ሓላፊዎች ጋር ውይይቶችን ያከናወነ መሆኑን ያስታወሰው ቦርዱ፤ በነዚህ ውይይቶች ላይ የምርጫ ኦፕሬሽን መዋቅር እና የክልል መስተዳድሮች የሚጠበቁ ሚናዎችን በዝርዝር አቅርቧል።
በውይይቶቹ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ቦርዱ የሚከተሉትን ዋና ዋና ትብብሮች ከክልል መንግሥታት ጠይቋል። እነርሱም፦
1. የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር- 33 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 3 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
2. ድሬደዋ ከተማ መስተዳድር- 47 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 1 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
3. ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት -72 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 11 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
4. ጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 14 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 3 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
5. ደ/ብ/ብ/ህ ክልላዊ መንግስት እና ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 132 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 17 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
6. ሃረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 3 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 1 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
7. አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት -32 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 5 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
8. አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 138 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 12 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች
9. ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት- 179 የምርጫ ክልል ቢሮዎች እና 20 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎች እና የስልጠና ቦታዎች መሆናቸውን ከመግለጫው ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY