ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጎንደር ከተማ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል 500 ሺሕ እንግዶች ይጠበቃሉ ተባለ።
በስፌራው በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የሚከበረውን የከተራ በዓል እና ጥር 11 የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ለማክበር ከ 500 ሺሕ በላይ እንግዶች ጎንደር ከተማ በመገኘት ይታደማሉ ተብሎ ከወዲሁ መገመቱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ከአጎራባች ቦታዎች ከሰሜን ከደቡብ ፣ እንዲሁም ከምዕራብ ጎንደር 300 ሺሕ ያህል እንግዶች እንደሚመጡ፤ እንዲሁም ቀሪዎቹ 200 ሺሕ ያህሉ ከሌሎች የሀገራችን ክልሎች እና ከውጭ ሀገር የሚመጡ ጎብኝዎች መሆናቸውን የገለጹት የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሓላፊ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው።