በአፋር ክልል አሳሳቢ የሆነ የአንበጣ መንጋ ተከሰተ

በአፋር ክልል አሳሳቢ የሆነ የአንበጣ መንጋ ተከሰተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአፋር ክልል ከፍተኛ የሆነ የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የበረሃ አንበጣ መከላከል ግብረ-ሃይል አስተባባሪ ዶክተር አያሌው ሹመት አፋምቦ፣ ዱብቲና አይሳኢታ ወረዳዎች ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የአንበጣ መንጋው ዳግም መከሰቱን አረጋግጧል።
መነሻውን ከጅቡቲ እና ሱማሌ ያደረገው የአንበጣ መንጋ በሌሎችም የክልሉ ወረዳዎች እየተስፋፋ ሲሆን፤ በክልሉ ሚሌ፣ ጭፍራ፣ ጉሊናና ቴሩ ወረዳዎች የአንበጣ መንጋው የተስፋፋባቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
አሁን ላይ በክልሉ የግብርና ሥራዎች የሚከናወኑበት ወቅት በመሆኑ የአንበጣ መንጋው ከእንስሳት መኖ በተጨማሪ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሕብረተሰቡን በማሳተፍ በባህላዊ መንገድ የመከላከል ሥራ እየተካሄደ ይገኛል ነው የተባለው። ከዚህ በተጨማሪ በሄሊኮፕተር የታገዘ የኬሚካል ርጭት ለማካሄድ መታሰቡም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY