ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያጣምረው መንገድ ግንባታ ነገ ይጀመራል

ኢትዮጵያን ከአሰብ ወደብ ጋር የሚያጣምረው መንገድ ግንባታ ነገ ይጀመራል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያን ከኤርትራ የአሰብ ወደብ ጋር የሚያጣምረው የሜሎዶኒ መገንጠያ ፣ ማንዳ – ቡሬ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ነገ በይፋ ይጀመራል ተባለ።

የሜሎዶኒ መገንጠያ – ማንዳ – ቡሬ መንገድ ሲጠናቀቅ ወደ አሰብ ወደብ የሚዘልቅ መንገድ በመሆኑ ለኢትዮጵያ የተሻለ የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሏል።
ፕሮጀክቱ 71 ነጥብ 65 ኪ.ሜ ርዝማኔ ሲኖረው የግባታው ሙሉ ወጪ 2,085,985,162.6 ብር የሚደርስ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚሸፈን ታውቋል።

LEAVE A REPLY