የቀድሞው ሜቴክ ወደ አትራፊነት ተሸጋግሪያለሁ አለ

የቀድሞው ሜቴክ ወደ አትራፊነት ተሸጋግሪያለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በህወሓት/ ኢሕአዴግ አመራር ለከፍተኛ ኪሳራ የተዳረገው የቀድሞው ሜቴክ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ 14 ሚሊየን ዶላር በላይ ከወጪ ንግድ አግኝቻለሁ አለ።

የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ንዑስ ዘርፍ በመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመቱ 14 ነጥብ 43 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከውጪ ንግድ መገኘቱ ነው የታወቀው።
በ2012 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት 20 ነጥብ አምስት ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቶ ነበር ያለው ተቋሙ፤
ይህም በያዝነው በጀት ዓመት ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር 29 ነጥብ ዘጠኝ በመቶ ቅናሽ እንዳሳየ እና በዶላር አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱን ገልጿል።

LEAVE A REPLY