ሁለት የህወሓት ዋነኛ ጀነራሎች እጅ ሰጡ

ሁለት የህወሓት ዋነኛ ጀነራሎች እጅ ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የህወሓት አባል የሆኑ፣ በትግራይ ክልል በመከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት የፈጸመውን ቡድን ሲመሩ የነበሩ ሁለት ጀነራሎች እጅ መስጠታቸው ተሰማ።

ለመከላከያ ሠራዊቱ በሰላም እጅ የሰጡት ሜጀር ጀነራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጀነራል ሙሉጌታ በርሄ ናቸው።
እነዚህ ሁለት ጀነራሎች ከትግሉ ጊዜ አንስቶ ዋነኛ የህወሓት አባል የነበሩ እና በለውጡ ማግስት በጡረታ የተሸኙ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ መቀሌ ከገቡ በኋላ በትግራይ ታጣቂ ኃይል በማጠናከር፣ የጥቃት እቅዶችን በመንደፍ እና በማስተባበር ሢሠሩ ቆይተዋል።

LEAVE A REPLY