ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮ ቴሌኮም የተፈቀደ ካፒታሉ ከ40 ቢሊየን ወደ 400 ቢሊየን ማደጉን ገለጸ።
ያለኝ ቋሚ ሀብት ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ አውቄያለሁኝ በማለት የተናገረው ኩባንያው፤ በቀጣይ የኩባንያው የቢዝነስ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ እያስጠናሁ ነውም ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ6 ወር ውስጥ 80.2 ሚሊየን የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በ2013 የመጀመሪያው መንፈቅ አመት 25.5 ቢሊየን ብር እንዳገኘም አስረድተዋል።
ገቢው ከሞባይል ድምፅ 49 በመቶ፣ በዓለም ዐቀፍ ከሚሰጡ አገልግሎቶች 10 በመቶ እና ከሌሎችም አገልግሎቶች መገኘቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል።
በ6 ወር ውስጥ የደንበኞቼ ቁጥር 50.7 ሚሊየን ደርሷል በማለት የተናገረው ኢትዮ ቴሌኮም፤ በዘንድሮው ግማሽ በጀት አመት 39.3 ቢሊየን ክፍያ አድርጊያለሁ፣ 16.2 ቢሊየን ብር ደግሞ ለመንግሥት ገብሬያለሁ ማለቱ ተሰምቷል።