ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት እነጃዋር መሐመድ ላይ ከቀረቡት ዐሥር ክሶች መካከል ፍርድ ቤቱ ሥድሥቱን ዛሬ ውድቅ አድርጓል።
ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞቹ ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል የሚጠቀሱ ሲሆኑ፤ በዛሬው ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና አያያዝ ጋር አስቀድመው በዐቃቤ ሕግ የተመሠረቱት ክሶች ናቸው።
ፍርድ ቤቱ “ኦነግ ሸኔ” የሚለው ስያሜ ምን እንደሆነ በተገቢው እንዲያብራራ በቀደመ ቀጠሮው መጠየቁን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ኦነግ ሸኔ ግለሰብ ሳይሆን ቡድን መሆኑን አስረድቷል።