አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ

አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከፍተኛ የሆነ የታጣቂዎች ጥቃት በሚፈጸምበት በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን አምስት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

እርምጃ ከተወሰደባቸው አምስት የሸኔ አባላት በተጨማሪ በርካታ ታጣቂዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዞኑ ጃል ያዴሳ ለተባለ የኦነግ ሸኔ አባል በባንክ በኩል ሊላክ የነበረ 122 ሺህ 950 ብር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል ያለው ፖሊስ፤ በቄለም ወለጋ ዞን እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታት የኅብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ፖሊስ በትጋት እየሠራ ይገኛል ብሏል።

LEAVE A REPLY