ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፖለቲካ ፓርቲዎች ለተመራጭ እጩዎቻቸው የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የሚያስገድደው ህግ በዚህ ዓመት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ።
ይህንን ጥያቄውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረበው ሲሆነ፣ ቀጣይ ውሳኔውም በፓርላማው የሚወሰን ይሆናል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ 1162/2011 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ለሀገራዊ ምርጫ 10,000፣ ለክልል ምክር ቤት ምርጫ ደግሞ 4,000 ፊርማ እንዲያሰባስቡ ያስገድዳል፡፡
ሆኖም በዚህ ወቅት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የወረቀት ልውውጥና ንክኪን ለመቀነስ በማሰብ የሚመለከተው የህጉ ድንጋጌ በዚህ ዓመት እንዲቀር ተጠይቋል፡፡