በርካታ የትህነግ የጦር መኮንኖች እጅ መስጠት እንደሚፈልጉ በደብዳቤ ገለጹ

በርካታ የትህነግ የጦር መኮንኖች እጅ መስጠት እንደሚፈልጉ በደብዳቤ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ረቡዕ ዕለት ለመከላከያ እጅ የሰጡት ሁለቱ የጁንታው ጀነራሎች  ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ መግባታቸው ታወቀ።

ለመከላከያ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሁለቱን ጀነራሎች ጨምሮ አንድ እጁን የሰጠ የጁንታው ኮለኔል ዛሬ አዲስ አበባ ገብተው ለምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የጁንታው አባላት የሆኑ የጦር መኮንኖች ለኮማንድ ፖስት ደብዳቤ በመላክ እጅ ለመስጠት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ታማኝ  ምንጮቹን በመግለጽ ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋ ማርያም በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል።
በስፍራው የሚገኘው ኮማንድ ፖስት የቀረበለትን ጥያቄ እንደተቀበለ ከከፍተኛ ጦር አዛዥ ማረጋገጡን የገለጸው፣ የህወሓትን ገመና ባለፉት ዐሥራ አምስት አመታት በማጋለጥ የሚታወቀው አርአያ ተስፋማርያም ፤ “የሚሻላቸው እጅ መስጠት ነው። ከዚህ በኃላ ሁሉም ነገር አብቅቷል” የሚል ምላሽ ከመከላያ አዛዦች ማግኘቱንም ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY