ታመዋል የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት አስተላለፉ

ታመዋል የተባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት አስተላለፉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በተለያዮ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በጸና መታመማቸው ሲነገር የዋለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና የሚናፈሰው ወሬም ሐሰተኛ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

የብልጽግና ሊቀመንበር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድም ዛሬ ከሰዐት በኋላ ጤንነታቸውን ለማመላከት ያለመ መልዕክት በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስነብበዋል።
ያለንን ዕምቅ ሀብት ተገንዝቦ ወደሚጨበጥ ተስፋ መቀየር የቆራጦች ተግባር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በዙሪያችን ኢትዮጵያ የያዘቻቸው እልፍ አእላፍ ዕድሎች አሉ። የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክም ከእነዚህ አንዱ ነው። ሠናይ እሑድ ይሁንልሽ ኢትዮጵያዬ!” ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ለሀገራቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY