አቶ ክቡር ገና እና ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ ኢዜማን ወክለው በቀጣዮ ምርጫ ይወዳደራሉ

አቶ ክቡር ገና እና ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ ኢዜማን ወክለው በቀጣዮ ምርጫ ይወዳደራሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በርካታ በሳል ፖለቲከኞችን ያሰባሰበው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)  ለሥድሥተኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ ቀጥሏል።

የታከለ ኡማ አስተዳደር በተረኝነት ፖለቲካ መንፈስ በዋና መዲናዋ የፈጸመውን ህገ ወጥ የመሬት  እና የኮንዶሚኒየም ቤቶች እደላን አስመልክቶ በቂ ጥናት የተደረገበት፣ ብሎም በማስረጃ የተደገፈ ሪፖርት በማቅረብ የሚሠራውን ሸፍጥ ያጋለጠው ኢዜማ በጊዜ ሂደት የደጋፊዎቹ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።
በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና በአንዷለም አራጌ የሚመራው ኢዜማ በምርጫው ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሻለ ሆኖ ለመገኘት አዳዲስ አባሎችን ወደ ድርጅቱ ቀላቅሏል።
በዚህም መሠረት አንጋፋው ምሁር እና ኢኮኖሚስት ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ክቡር ገና በቀጣዮ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ኢዜማን ወክለው እንደሚወዳደሩ ተሰምቷል።
ወረዳ ሦስትን ወክለው የሚወዳደሩት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ አንዷለም አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋን የመሳሰሉ ሀቀኛ ፖለቲከኞችን የሰበሰበው ኢዜማ ከወዲሁ በአዲስ አበቤዎች ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ነው ተብሎለታል።

LEAVE A REPLY